OR Department Head Nurse 60 views

Company Profile

St. Gabriel General Hospital was established in September 1996 and is the first private hospital of its kind in Ethiopia. St. Gabriel General Hospital has paved the way and continues to provide access to healthcare to both the local and international community’s here in Addis. Over the past 22 years, the hospital has served over 300,000 patients in both Outpatient and Inpatient departments.

Our vision

We aim to deliver exceptional healthcare in a safe, compassionate, and caring environment that meets international standards. As a role model, Saint Gabriel Hospital has and will continue to pave the way to accessible quality healthcare to both the local and international community.

የሥራ መደቡ ዋና ዋና ተግባራት

ከሜትረን የሚሰጡትን ትዕዛዞች በመቀበል ለህመምተኞች አስፈላጊውን ህክምናና እንክብካቤ ያደርጋል፤ ወደ ሆስፒታሉ ቀደም ብሎ በመግባት በስሩ የሚገኙ ነርሶች ስራቸው ላይ መገኘታቸውን ይቆጣጠራል እንዲሁም  ህመምተኞች ሌሊቱን እንዴት እንዳደሩ አስፈላጊውን መረጃ ከአዳሪ ነርስ ይቀበላል፤ ከሃኪሞች ጋር አብሮ የበሽተኞች ጉብኝት በማድረግ የሃኪሙን ትዕዛዝ ይቀበላል፤ ለህመምተኛው የታዘዙ መድሃኒቶች በካርድ ላይ መስፈራቸውን ያረጋግጣል፣ ህሙማን ከሆስፒታል ሲወጡ የአገልግሎት ክፍያ መፈፀማቸውንና ንብረት ማስረከባቸውን ያረጋግጣል፡፡

የስራ መደቡ ዝርዝር ተግባራት

1.      በመግቢያ ሰዓት ቀደም ብሎ በመግባት ህመምተኞችን የአዳር ሁኔታ ይጠይቃል ይከታተላል፣ የህመምተኞች አልጋ አካባቢ ያለውን ንፅህና ይቆጣጠራል፣ መኝታቸው በፈሻስ አለመበላሸቱን ፣ድሪፕ ካለው አለማበጡንና መሳሰሉትን ተከታትሎ ቸግር ካለ ከአዳሪ ነርስ ጋር በመሆን ችግሩን ያስወግዳል፡፡

2.     በስሩ የሚገኙ ነርሶች የስራ ሰአታቸውን አክብረው መገኘታቸውን ይቆጣጠራል፡፡ አርፍደው የሚመጡ ነርሶች ላይ ከምክርና ከቃል ማስጠንቀቂያ ጀምሮ ተገቢውን የእርምትና የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፡፡በተደጋጋሚ ያሚያረፍዱ ሲኖሩም ሪፖርት ያደርጋል፡፡

3.     ያለፈቃድ ከስራ የሚቀሩ ነርሶች ሲያጋጥሙ ከግማሽ ቀን ባልበለጠ ጊዜ ለአስተዳደር ሪፖርት ያደርጋል፡፡

4.     በስሩ የሚገኙት ነርሶች ሲገቡም ካደሩት ነርሶች ጋር ተሰብስቦ አዳሪ ነርሶች የጻፏቸውን ሪፖርት በማንበብ ውይይት ያካሂዳል፤ቀጣይ ስራዎች ካሉ በአስቸኳይ እንዲፈፀሙ ያደርጋል፡፡

5.     በስሩ ላሉት ነርሶች፣ ጤና ረዳቶችና አስታማሚዎች የሥራ ክፍፍል ያደርጋል፡፡ሠራተኞች ስራቸውን በተሰጣቸው ፕሮግራም መሰረት ማከናወናቸውን ይቆጣጠራል፡፡

6.     ሀኪሞች ጉብኝት ሲያደርጉ አብሮ በመገኘት የህመምተኞችን ሁኔታ ይረዳል፣ የታዘዘውን ትዕዛዝ ሁሉ በአግባቡ ተረድቶ ተግባራዊ መሆኑን ወይም በስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፡፡

7.     የህመምተኞች መድሃኒት ሳያልቅ በወቅቱ እንዲተካ ያደርጋል፤ ለድንገተኛ የሚቀመጡ መጠባበቂያ መድሃኒቶች እንዲሟሉ ያደርጋል፡፡

8.     የናርኮቲክ መድሃኒት ለማን እንደተሰጠ ለይቶ ማወቅና ከተሰጠም መፈረሙን ያረጋግጣል፡፡

9.     ከህመምተኞች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በትዕግስት በማዳመጥ ቅሬታዎቹ እንዲወገዱ አሰፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፤ ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ ከሆነ ለሚመለከተው ክፍል ያሳውቃል፡፡

10.   የመኝታ ክፍሎችና የህክምና ክፍሎች ንፅህና በሚገባ መጠበቁን በማረጋገጥ አስፈላጊ የሆኑ አልባሳትና መገልገያዎች እንዲሁም የህክምና መሳሪያዎች የተሟሉ መሆኑን ይከታተላል፣ያረጋግጣል፡፡

 

11.     ህመምተኞች ተኝተው እንዲታከሙ ሀኪም ሲያዝ ህመምተኛውን ትህትና በተሞላበት መንገድ መቀበልና አስፈላገው እርዳታ ወዲያውኑ እንዲጀመር ያደርጋል፡፡

12.    ለህመምተኞች የተሰጡ መድሃኒቶችና አገልግሎቶች በህሙማን ካርዶች ላይ በወቅቱ መሞላታቸውን ማረጋገጥ፣ ህሙማኑ ከሆስፒታል እንዲወጡ ሀኪም ሲያዝ ለተሰጡት አገልግሎቶች ተገቢ ክፍያ መፈፀሙንና በመኝታ ክፍል ያሉ ንብረቶች በተገቢው ሁኔታና መጠን መኖራቸውን ያረጋግጣል፡፡

13.    የሆስፒታሉን ንብረቶች በእንክብካቤ መያዛቸውን የመቆጣጠር፣ የመጠበቅና የመንከባከብ ኃላፊነት እንዳለበት ተገንዝቦ ይህንኑ በስሩ ለሚገኙት ሠራተኞች ያሳውቃል፡፡ በማንኛውም ጊዜ የንብረት ርክክብ በትክክል መፈፀሙን ይቆጣጠራል፡፡

14.   የሠራተኞችን የስራ አፈፃፀም ለመገምገም የሚያስችሉ መረጃዎችን ይይዛል፤ ድርጅቱ በሚያወጣው ፕሮግራም መሰረት የሥራ አፈፃፀማቸውን ይሞላል፣ ለአስተዳደር በወቅቱ ያስተላልፋል፡፡

15.    ተረኛ ነርስ ወይም ሠራተኛ በሥራ ላይ መገኘት ባይችል በወቅቱ ፕሮግራሙን አስተካክሎ ሠራተኛ ይመድባል፤ሠራተኛ መመደብ በማይቻልበት ጊዜ እራሱ የቀረውን ሠራተኛ ቦታ ሸፍኖ ይሰራል፡፡

16.   በየስድስት(6) ወሩ የህመምተኞችን ስታስቲካዊ መግለጫ እየሞላ አግባብ ላለው ክፍል ያስተላልፋል፡፡

17.    ከአስተዳደር የሚላኩትን ማስታወቂያዎችም ሆነ ሌላ ማስታወሻ ለሠራተኞች በግልፅ ቦታ እንዲለጠፍና መልዕክቱ እንዲደርስ ያደርጋል የተባለውም በስራ ላይ መዋሉን ያረጋግጣል፡፡

18.   በኃላፊ ነርሶች ስብሰባ ላይ በሠራተኞች እንዲተላለፍ የተነገረን መልዕክት ወዲያውኑ በስሩ የሚገኙትን ሰራተኞች ሰብስቦ ማስረዳትና ተግባራዊነቱን መከታተል፡፡

19.   በየጊዜው በስሩ ከተመደቡት ሠራተኞች ጋር በመወያየት ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ወቅቱን የጠበቀ የእርምት እርምጃዎችን ይወስዳል፣ በቡድኑ የመማማር እና የመረዳዳት ባህል እንዲኖር የራሱን አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡

20.  በነርስ ኃላፊዎች ስብሰባ ላይ ይሳተፋል፡፡

21.    ለክፍሉ የሚያስፈልጉ አላቂና ቋሚ ዕቃዎችን በወቅቱ ይጠይቃል፡፡

22.   አዳዲስ ግኝቶችና የቴክኖሎጂ ለውጦች ሲኖሩ ራሱንና በስሩ የሚገኙትን ሠራተኞች እንዲያውቁ ያደርጋል፡፡

23.   ከቅርብ ኃላፊው የሚሰጡ ሌሎች ተጨማሪ  ተግባራትን ያከናውናል፡፡

Job Requirements

  • BSc Degree in Nursing
  • A minimum of 5/8 years and above in Hospital from which at least 3 years experience as a Head nurse in the same department
  • Up-to-date health professional License Certificate is mandatory.
  • Basic Computer skill

How to Apply

All applicants should send a Curriculum vitae, Educational records, Work certificates & Valid Professional license either by email to [email protected] or non-returnable copies of credential to St. Gabriel General Hospital HR Office numebr 112

Addis Ababa, 22 Mazoria on the way to Bole Medhaniyalem Church in front of Awraris Hotel 

Please note that only short-listed applicants will be contacted

More Information

  • This job has expired!
Email Me Jobs Like These
Showing 1–0 of 0 jobs

Leave your thoughts

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

Share this job
Company Information
Contact Us
https://justjobset.com/wp-content/themes/noo-jobmonster/framework/functions/noo-captcha.php?code=4bf9f

Newsletter